EthiopiaNews

በዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል አንድ እናት ሶስት መንታዎችን በሰላም እንደተገላገሉ የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

ወይዘሮ አሲያ ሁሴን የተባሉ እናት በትናንትናው እለት ሶስት መንታዎችን በአፋር ክልል የዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል በሰላም ተገላግለዋል።

በአሁኑ ሰዓት የእናትየውም ሆነ የሶስቱ አዲስ ጨቅላ ህፃናት ጤንነት ሙሉ በሙሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሆስፒታሉ ገልጿል።

ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ሶስት መንታዎች በአንድ ላይ ሲወለዱ በሆስፒታሉ ታሪክ ይህ የመጀመሪያው ክስተት ነው ተብሏል።መረጃው ከአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።