አሜሪካ የህዋ ምርምር ተቋሟ ናሳን ጨምሮ በርካታ የፌደራል ተቋማቷ በቻይና እንደተሰለሉባት ከሰሰች።
አሜሪካ እንደምትለው በቻይና መንግስት የሚደገፉት የመረጃ መረብ ሰባሪዎች ናቸው በናሳና በብሔራዊ ባንኳ እንዲሁም በሌሎች ቁልፍ የመንግስት ተቋማት ላይ የመረጃ ምዝበራ ያካሄዱት።
ይሁንና የአሜሪካ ባለስልጣናት ምን ያህል ከባድ ሚስጥሮች እንደተዘረፉ የገለፁት ነገር የለም።
አሜሪካ ይሄን ክስ ያቀረበችውም ፕሬዝዳንት ትራምፕና የቻይናው አቻቸው ከሳምንት በኋላ በዋሽንግተን ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነው። ይሁንና ቻይና ክሱን ነጭ ውሸት ስትል ውድቅ አድርጋዋለች።
በዋሽንግተን የቻይና ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ቤጂንግ ማንኛውንም የሳይበር ጥቃት ታወግዛለች ብሏል።
