EthiopiaNews

ለአጠቃላይ ቀዶ ጥገና፣ ለፕላስቲክ ቀዶ ጥገና እና ከአፍ ጤና ሕክምና ጋር የተያያዙ ቁሳቁሶችን የሚያመርተው የቻይናው ሺጃንግ ወዱ ሜዲካል ኩባንያ ወደ ቂሊንቶ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ሊገባ በሚችልበት አግባብ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

የኩባንያውን ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር በዚሁ ጉዳይ የመከሩ ሲሆን ሺጃንግ ወዱ ሜዲካል ኩባንያ በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ለመገንባት ከወሰነ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ይደረግለታል ነው የተባለው፡፡

ኩባንያው በአውሮፓውያኑ 1975 የተመሠረተውና በቻይና ካሉ ትልልቅ የግል ተቋማት አንዱ የሆነው ሄንግዲያን ግሩፕ አካል ሲሆን ግሩፑ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶች፣ የፋርማሲና ጤና መጠበቂያ ምርቶች በማምረት የሚታወቅ ነው።