EthiopiaNews

በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በቴሌ ብር መተግበሪያ የ4 ነጥብ 19 ትሪሊየን ብር የዲጅታል ግብይት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አስታወቀ።

ኢንቨስትመንት ሆልዲንግሱ ይሄንን ያለው በስሩ የሚገኙ ተቋማት አመታዊ አፈጻጸም ግምገማ ለ3ኛ ቀን መቀጠሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው።

የቴሌ ብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ60 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ያነሳው ተቋሙ ቴሌ ብር በ2018 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 83 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንም ገልጿል።

በተጨማሪም በበጀት አመቱ የኢትዮ ቴሌኮም ገቢ በ33 ነጥብ 2 በመቶ ማደጉም ነው የተጠቀሰው።