EthiopiaNews

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 15 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱ ተነገረ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ይሄንን ያለው በስሩ የሚገኙ ተቋማት አመታዊ አፈጻጸም ግምገማ ለ4ኛ ቀን መቀጠሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው።

ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ያገኘው ገቢ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ35 በመቶ ጭማሬ እንዳለው ነው የተገለጸው፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በበጀት አመቱ 438 ሺ 140 ኩንታል ምርጥ ዘር ማምረቱ እና ከ2 ሚሊየን በላይ ኩንታል ማዳበሪያ ማሰራጨቱን ገልጿል።መረጃው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv