የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካናዳው ኦንታሪዮ ሐይቅ ስም ተቀይሮ የአሜሪካ ሐይቅ እንዲባል ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ሰጡ።
ሐይቁ በካናዳዋ የኦንታርዮ ግዛት ሲገኝ ከአሜሪካዋ የኒውዮርክ ግዛት ጋር ይዋሰናል።
ትራምፕ በተናጠል ውሳኔውን የሰጡት አገራቸው ከካናዳ ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ በገባች ማግስት ነው።
በዚሁ የንግድ ጦርነት አሜሪካ 20 ቢሊዮን ዶላር በሚያወጡ የካናዳ ምርቶች ላይ የ50 ከመቶ ታሪፍ ስትጥል ካናዳም ተመጣጣኝ ታሪፍ ለመጣል ተሰናድታለች።
የሐይቁን የስያሜ ለውጥ በተመለከተ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔ የኦንታሪዮ ሐይቅ ዛሬም ሆነ ወደፊት ኦንታሪዮ የሚለውን ስያሜ ይዞ ይቀጥላል ብለዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
