EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ህጋዊ እውቅና የሌላቸውን 17 የሃዋላ አስተላላፊዎች ዝርዝር ይፋ አደረገ።

ባንኩ ዝርዝሩን ይፋ ያደረገው ህገ ወጥ የሃዋላ አስተላላፊዎችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ሲሆን በህገወጥ የሃዋላ አስተላላፊዎች በኩል ገንዘብ ማስተላለፍ ለአደጋ የሚያጋልጥና የሕግ ተጠያቂነት የሚያመጣ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡

አማና ኤክፕረስ፣ አዱሊስ  መኒ ትራንስፈር፣ ወርልድ ዳይሬትሊንክን ጨምሮ 17 የሃዋላ አስተላላፊዎች ህጋዊ እውቅና የሌላቸው መሆኑን የገለጸው ባንኩ ማህበረሰቡ እነዚህ የሃዋላ አስተላላፊዎች ህገወጥ መሆናቸውን አውቆ በተቋማቱ ገንዘብ ከመላክ እንዲቆጠብም አሳስቧል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv