የአለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሃምሌ ወር ብቻ በኢትዮጵያ ለ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ኘሮግራሙ ይሄን ያለው በኢትዮጵያ እያካሄደ ያለውን ድጋፍ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ ሲሆን ለ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎች 13 ሺህ 8 መቶ ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍ ማድረጉንም ነው የገለጸው።
በተጨማሪም ለእነዚህ ዜጎች ከ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር በላይ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጋለሁ ያለው የአለም ምግብ ፕሮግራም በጋምቤላ ክልል የሚገኙ 90 ሺህ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችንም እያገዘ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ በመጪዎቹ 6 ወራት በቂ ድጋፍ ለማድረግ 300 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው የገለጸው ፕሮግራሙ በቀጣይ 3 ወራት በሰሜን ኢትዮጵያ ብቻ ለሚገኙ 176 ሺህ ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱንም በመግለጫው አስፍሯል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
