የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ሀይል የማመንጨት አቅም 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
ተቋሙ ይህንን የገለጸው የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድን በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲሆን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ መግባት እንዲሁም የአሰላ እና የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ወደ ኦፕሬሽን መግባታቸው ለኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም መጨመር አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት 124 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ መሰብሰቡን ያስታወቀው ተቋሙ ከተገኘው ጠቅላላ ገቢ ውስጥ 39 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብሩ የተጣራ ትርፍ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ከ475 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ መሰብሰብ መቻሉንም ገልጿል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
