InternationalNews

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮንደርለይን አህጉሩ ከሩሲያ ሲገዛ የነበረውን ርካሽ ነዳጅ በመቆሙ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን ገለጸዋል።

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አሁን ላይ እጅግ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ለመክፈል መገደዳቸውን የገለጹት ፕሬዝዳንቷ ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ የሩሲያን ነዳጅ ላለመግዛት የተወሰነው ውሳኔ በአህጉሩን ኢኮኖሚ እየፈተነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢራንን ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋን ከሚገመተው በላይ እንዳናረው የገለጹት ኡርሱላ ቮንደርለይን ይህም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት እድገት ላይ ከባድ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv