ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን በነባር እና አዲስ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ለፈተና የተመረጡ ተማሪዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ሚነስቴሩ ይሄን ያለው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ይፋ መደረጉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
በዚሁ መሠረት ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተማሪዎች በተመዘገቡበት የበየነ መረብ መስፈንጠሪያ (ሊንክ) የመለያ ኮዳቸውን በማስገባት ለፈተና መመረጣቸውን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ፈተናው በበየነ መረብ (ኦንላይን) የሚሰጥ በመኾኑ ለፈተና የተመረጡ ተማሪዎች የሚቀርባቸውን የፈተና መስጫ ማዕከል በዚሁ ሊንክ ገብተው መምረጥ እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ሚኒስቴሩ የሙከራ ፈተና ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም እንዲሁም ዋና ፈተና ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል።
በመኾኑም ተማሪዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
