አፍሪካ በአየር ንብረት መዛባት ምከንያት ተደጋጋሚ ድርቅ፣ ጎርፍ እና ሌሎች አደጋዎችን እያስተናገደች መሆኑ ተነገረ፡፡
ይህ የተነገረው ለ3 ቀናት የሚቆየው የአፍሪካ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ፎረም በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረበት ወቅት ነው፡፡
በፎረሙ ኢትዮጵያ በቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎች ዙሪያ ከአፍሪካ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራች እንደምትገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ፎረሙ በአፍሪካ የአየር ንብረትና የተፈጥሮ አደጋዎች ስጋትን ለመቀነስ የቅድመ ማስጠንቀቂያና የቅድመ እርምጃ ሥርዓቶችን ለማጠናከር እንዲሁም ዘላቂ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅሞችን ለማሳደግ ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
