የአማራ ክልል በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 357 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረቡን አስታወቀ።
የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ ይሄን ያለው በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ መድረክ ላይ ነው።
የቢሮውኀላፊ ኃይሌ አበበ በባለፈው የ2018 በጀት ዓመት ከወርቅ ወደ 64 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
ኃላፊው በተያዘው የ2019 በጀት ዓመት ክልሉ 1ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ ማቀዱን አስታውቀዋል።መረጃው ከአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።
