የጤና ሚኒስቴር በፈረንጆቹ 2030 አመት ኤች አይቪ ኤድስ የማህበረሰብ የጤና ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ እንዲደርስ ግብ መያዙን አስታወቀ።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ይሄን ያሉት በኔፕ ፕላስ 21ኛ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ነው።
ሚኒስትር ዴኤታው በፈረንጆቹ በ2030 አመት ኤች አይቪ ኤድስ የማህበረሰብ የጤና ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ እንዲደርስ የተያዘዉን ግብ ለማሳካት ሁሉም በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ዶ/ር ደረጀ ኤች አይቪ ኤድስን በመከላከልና ለመቆጣጠር በተደረገዉ ርብርብ ዉስጥ ኔፕ ፕላስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዉ ኤች አይቪ ኤድስን በመከላከልና ለመቆጣጠር እስካሁን በተሰሩ ስራዎች የተገኙ ዉጤቶችን በደምብ በመቀመር፣ያገጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየትና በሽታዉን ለመግታት የተነደፉ ስትራቴጂዎችን በአግባቡ በመተግበር የተያዘዉን ግብ ማሳካት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዉ አሁንም የህብረተሰቡን ግንዛቤ የሚያሳድጉ ስራዎች ተጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ በማሳሰሰብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም ለወጣቶችና ሴቶች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የመለየትና ምርመራ ፣ አስፈላጊዉን ግብዓት ሟሟላትና ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ የሚገኙ ወገኖችን መንከባከብ ያስፈልጋል ብለዋል።
