EthiopiaNews

የአሜሪካ የዜግነት እና ኢምግሬሽን አገልግሎት በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ቢሮውን ሊከፍት መሆኑን ይፋ አደረገ።

አገልግሎቱ ይሄን ያለው የአዲስ አበባ አለም አቀፍ ቢሮው ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ሥራውን እንደሚጀምር ባወጣው መግለጫ ነው።

የኢትዮጵያ ቢሮው በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን እንደሚከታተል ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው።

አዲሱ ቢሮ የውጭ ሰነዶችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣ የተጠረጠሩ ማጭበርበሮችን መመርመር እና የቤተሰብ ዝምድናዎችን ለማረጋገጥ የዲኤንኤ ናሙናዎችን የመሰብሰብ ኃላፊነቶችን እንደሚወጣ ተገልጿል።

ተቋሙ ቀደም ሲል እነዚህ አገልግሎቶች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ጋር በመተባበር ይከናወኑ እንደነበር አስታውሶ አዲሱ ቢሮ የተሰጠውን ኃላፊነት በቀጥታ ለመወጣት ያስችለኛል ብሏል።መረጃው ከአሜሪካ የዜግነት እና ኢምግሬሽን አገልግሎት የተገኘ ነው።