የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሃሳቦችን በማደራጀት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከሐምሌ 01 ቀን እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን ያካሄደው ኮሚሽኑ በሂደቱ የተገኙ በርካታ ምክረ-ሃሳቦችን በየፈርጃቸው እያደራጀ መሆኑንም ነው የጠቀሰው፡፡
ኮሚሽኑ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት በአሁኑ ሰዓት ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሃሳቦችን በየፈርጁ ካደራጀ በኋላ በቀጣይ ምክረ-ሃሳቦቹን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብም ይፋ አድርጓል፡፡
ከዚያም እነዚህን ምክረ-ሃሳቦች ለሕዝብ ይፋ አደርጋለሁ ያለው ኮሚሽኑ በመጨረሻም ምክረ-ሃሳቦቹን ለአስፈፃሚ በማቅረብ ተፈፃሚነታቸውን እንደሚከታተል ይጠበቃል፡፡
