EthiopiaNews

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ 840 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 840 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩና በሕግ በተደነገገው አግባብ የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ መንግስት የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የሕግ ታራሚዎቹ በመደበኛ የይቅርታ ሕግ እና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተብለዉ በልዩ ሁኔታ የቀረቡ፤ በማረሚያ ቆይታቸው ስለመታረማቸውና ስለመታነፃቸው ማረጋገጫ የቀረበላቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መሰረት የይቅርታው ተጠቃሚዎች በይቅርታ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት አዋጅ እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው፡ በማረሚያ ቤት የቆዩ፤ በጤና ችግር፤ በዕድሜ መግፋትና ከሕጻናት ጋር አብረዉ የታሰሩ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

ህብረተሰቡም ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በፈፀሙት ጥፋት የተፀፀቱና በአግባቡ ታርመው የወጡ መሆኑን በመረዳት መልካምና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላቸው ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል