EthiopiaNews

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 13 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ለማመንጨት ማቀዷን ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በዓመታዊው ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በዚህ ንግግራቸው ኢትዮጵያ ከንጹህ ኃይል ብቻ 60 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንዳላት ገልጸዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ የንጹህ ኃይል ልማቷን በማጠናከር ለጎረቤት ሀገራት የምታቀርበውን የኃይል መጠን ለማሳደግ እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ፣ በታዳጊና በበለጸጉ ሀገራት መካከል የንግድ ትስስር መፍጠርና በቴክኖሎጂ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እንዲሁም በዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ኢንቨስትመንቶችን ማፋጠንን አላማው ያደረገው ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ በዱባይ እየተካሄደ ይገኛል፡፡