የአዲስ አበባ ልኳንዳ ቤቶች ማህበር በመጪው አዲስ ዓመት በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ስጋ ቤቶች 1 ኪሎ የበሬ ስጋ በ1 ሺህ 200 ብር ለህብረተሰቡ እንደሚቀርብ አስታውቋል።
ይህ የተነገረው የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በመዲናዋ ከ4 ሺህ 500 በላይ የቁም እንስሳት እርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስመልክቶ ትናንት በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።
ለመጭው የዘመን መለወጫ በዓል የስጋ አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር እስከ 50 ሺ የቁም እንስሳት ወደ ከተማዋ እየገቡ እንደሚገኝ በመግለጫው የተነገረ ሲሆን ባለፉት በዓላት ከዋጋ ጋር በተያያዘ በሸማቾች ስራ ማህበራት ልኳንዳ ቤቶች የተፈጠረን የምርት እጥረትና በጊዜ ጨርሰናል የማለት አዝማሚያ ለማስቀረት የዋጋ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ልኳንዳ ቤቶች ከከተማዋ ሃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት የአንድ ኪሎ ስጋ ዋጋ 1200 ብር መተመኑን ገልፆ ማህበረሰቡ ከሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ስጋ ቤቶች በዚሁ ዋጋ አገልግሎት ማግኘት ይችላል ተብሏል።
በመሆኑም ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ ጥራትና ደህነንቱ በተጠበቀ መልኩ በግና ፍየልን በ300 ብር፣ እንዲሁም በሬን ደግሞ በ2ሺ አንድ መቶ ብር በቄራ ድርጅቶች የእርድ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል መገለፁ ይታወሳል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
