EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአፍሪካ ካሉ 30 ትልልቅ ባንኮች መካከል በጠቅላላ ሀብት መጠን 15ኛ ደረጃ መያዙን አስታወቀ።

ባንኩ ይሄን ያለው በአፍሪካ ያለውን ደረጃ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ነው።

በአፍሪካ ትሬድ ፋይናንስ ካምፓኒ በቀረበው የ2026 መረጃ መሠረት ባንኩ በጠቅላላ 25 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በመያዝ ከአፍሪካ ትልልቅ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ 15ኛ ደረጃን ላይ መስፈሩን ገልጿል።

በዝርዝሩ ላይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በላይ የተቀመጡት ባንኮች የደቡብ አፍሪካ፣ የግብፅና የሞሮኮ ባንኮች ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያን ባንክ ዘርፍን በመወከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛው ባንክ ነው ተብሏል።

ንግድ ባንክ በአፍሪካ የፋይናንስ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን ስም በከፍተኛ ደረጃ የሚያስጠራ ስኬት ማስመዝገቡ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ መምጣቱን እና የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም መስፋፋቱን ያሳያል ብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአህጉሩ የባንክ ዘርፍ እየጨመረ ባለው ውድድር የባንኩ ቀጣይ ጉዞ ደግሞ የሀብት መጠንን ብቻ ሳይሆን የዲጂታል ባንኪንግ፣ የፋይናንስ ፈጠራ፣ የአህጉራዊ ግንኙነት እና የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት አቅሙን ማሳደግ ይሆናል ብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv