የኬንያ መንግስት በሃገሪቱ ያለሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሚኖሩ የምስራቅ አፍሪካ ዜጎች እራሳቸውን እንዲያስመዘግቡ የሚያስችል ተጨማሪ ጊዜ ሰጠ።
ይህ ውሳኔ የተሰማው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ያለፈቃድ የሚንቀሳቀሱ ውስን የውጭ ሃገር ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ እርምጃው ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በናይሮቢ በሚኖሩ የአካባቢው አገራት ዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮ ነበር ተብሏል።
የኬንያ መንግስት በበኩሉ በውጭ ሃገራት ዜጎች ላይ የሚፈጸምን ማንኛውንም አይነት ጥቃትና ማስፈራሪያ እንደማይታገስ ገልጾ፣ በዚህ የምዝገባ ወቅት ራሳቸውን የሚያስመዘግቡ ዜጎች ሕጋዊ እውቅና ተሰጥቷቸው የህክምናና የባንክ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ አረጋግጧል።
የፕሬዝዳንት ሩቶ ተችዎች በበኩላቸው መንግስት በመጭው ዓመት የሚካሄደውን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ውድቀት በውጭ ሃገር ዜጎች ላይ ለማሳበብ እየሞከረ ነው በማለት እየከሰሱ ይገኛሉ።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
