InternationalNews

የፈረንሳይ ታዋቂው የቱሪስት መዳረሻ የሆነው የኢፍል ታዎር፣ ሰራተኞቹ ባደረጉት የሥራ ማቆም አድማ ምክንያት ክትላንት ጀምሮ ለጎብኝዎች መዘጋቱ ተሰማ።

ለአድማው መነሻ የሆነው፣ ባለፈው ቅዳሜ ታዎሩን የጎበኙ የሂንዱ ሃይማኖት ተከታዮችን ለማስተናገድ ሲባል፣ ሴት ሰራተኞች ከስራ ቦታቸው ገለል እንዲሉ በመደረጉ እንደሆነ ነው የተነገረው።

100 የሚሆኑት የሂንዱ እምነት ልዑካን ቡድኑ አባላት ‘ከሴቶች ጋር ንክኪ እንዳይኖረን’ በሚል ባቀረቡት ጥያቄ፣ አስተዳደሩ ሴት ሰራተኞችን በወንዶች እንዲተኩ ማድረጉ በሰራተኞቹ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቷል።

የሰራተኛ ማህበሩ ድርጊቱን አሳፋሪ ሲል ያወገዘው ሲሆን፣ የኢፍል ታዎር አስተዳዳሪ ኩባንያ በበኩሉ የተፈጠረው ስህተት ከጾታ እኩልነት መርህ ጋር የሚቃረን መሆኑን አምኖ ይቅርታ ጠይቋል ተብሏል።

የፓሪስ ከንቲባን ጨምሮ ከፍተኛ የፈረንሳይ ፖለቲከኞችም ክስተቱን በጽኑ የኮነኑ ሲሆን፣ በየትኛውም ታሪካዊ ስፍራም ሆነ የሃገሪቱ ክፍል የጾታ እኩልነት ሊጣስ እንደማይገባ በማሳሰብ በጉዳዩ ላይ ጥብቅ ምርመራ እንዲጀመር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ነው የተባለው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv