የአሜሪካ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ አካባቢ ለሚገኙ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ብድር ለማቅረብ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ለመመደብ ማቀዱ ተነግሯል፡፡
ይህ የተገለጸው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ፍራንክ ጋርሺያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ጋር በአቪዬሽን ዘርፍ ያለውን ግንኙነትና አየር መንገዱ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ያለውን አጋርነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በመከሩበት ወቅት ነው።
በዚሁ ወቅትም በቢሾፍቱ እየተገነባ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን የጎበኙት ረዳት ሚኒስትሩ በፕሮጀክቱ ለመሳተፍ የአሜሪካ ኩባንያዎች ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡
የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትሩ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር የኢትዮጵያና አሜሪካን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸው የሚታወስ ነው፡፡
የሁለቱ ባለሥልጣናት ውይይት፣ በቀጠናዊ ሰላምና ጸጥታ ላይ ጭምር ያተኮረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጿል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
