InternationalNews

ካናዳ፣ 28 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር ግምት ባላቸው የአሜሪካ ምርቶች ላይ የጣለችው እስከ 50 በመቶ  የሚደርስ የአጻፋ ታሪፍ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ሥራ ላይ ውሏል።

ይህ የታሪፍ ጭማሪ በብረት፣ በቤት ቁሳቁሶችና በጨርቃጨርቅ ምርቶች ላይ የተጣለ ሲሆን፣ እርምጃው የተወሰደው በሁለቱ ሃገራት መካከል ይደረግ የነበረው የንግድ ድርድር ያለስምምነት መቋረጡን ተከትሎ ነው።

በታሪፍ ጦርነቱ ምክንያት ለሚጎዱ የካናዳ አነስተኛና መካከለኛ ኩባንያዎች እንዲሁም ሰራተኞች  የሚሆን በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀፍ በመንግስት በኩል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ ሃገራቸው ፍትሃዊ ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ቢናገሩም፣ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በካናዳው ቦምባርዲየር ኩባንያ ላይ ተጨማሪ እገዳ እንደሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል።

ይህ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረው የንግድ ጦርነት፣ በሸማቾች ላይ የዋጋ ጭማሪን ከማስከተሉም በላይ በሃገራቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv