InternationalNews

አሜሪካ በአምስት የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት ስትፈፅም አንዱ መርከብ መስመጡ ተነግሯል።

ይህንኑ የአሜሪካ ጥቃት ተከትሎ ኢራን በዮርዳኖስ በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ የአፀፋ ጥቃት ፈፅማለች።

የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ እንዳለው አራቱ የኢራን ዕቃ ጫኝ መርከቦች ኢላማ ውስጥ የገቡት በኦማን ሰርጥ በባህር ላይ ሲቀዝፉ ነው። አንደኛው መርከብ በካርግ የኢራን ደሴት አካባቢ መመታቱን ነው ያስታወቀው።

ሁለቱ አገራት የሚፈፅሙት ጥቃትና የአፀፋ ጥቃት ባለፉት ሳምንታት የተጠናከሩ ሲሆን አሁን ኢራን በሰርጡ አካባቢ ያሉ ወደቦች በሚገኙ መርከቦች የሚሰሩ ባህርተኞች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እያስጠነቀቀች ነው።