EthiopiaNews

የእስያ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ በትብብር ለመስራት መስማማቱ ተገለጸ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከባንኩ ፕሬዚዳንት ዙ ዥያይ ጋር በተለይም በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ላይ የሚኖር ተሳትፎን በተመለከተ እንዲሁም በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር በኢነርጂ እና በአየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም ባንኩ ለኢትዮጵያ ተመጣጣኝ የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የእስያ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ የሚገነቡ የመሰረተ ልማቶችን በፋይናንስ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑ በውይይቱ ወቅት መግለጽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡