InternationalNews

የየመን ሀውቲዎች የአገሪቱን የባህር ጠረፍ መቆጣጠራቸው የአካባቢውን የኃይል ሚዛን አዛብቶታል ተባለ።

ሀውቲዎች ሰሞኑን በፈፀሙት ፈጣን ማጥቃት ወሳኙን የባብል መንደብን በቅርብ ርቀት መቆጣጠራቸውና ሌሎች የባህር ዳርቻ ይዞታዎችን መያዛቸው እንደ ሳዑዲ አረብያ ያሉ የሰላጤው አገራት የባህር አማራጭን ጥያቄ ውስጥ ከቶታል።

ሳዑዲ አረብያ በኢራን ጦርነት ሳቢያ የነዳጅ ወጭ ምርቷን ከሆርሙዝ ወደ ቀይባህር ብታዞርም አሁን ቀይ ባህርን ተጠቅማ ወደ እስያ ለምትልከው ነዳጅ ሌላ ተጨማሪ ወጭ ጠይቋታል።

የሀውቲዎች አላማም ሆርሙዝ በኢራን ስለተዘጋ አሁን ቀይ ባህርን በመዝጋትና የዓለም ነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር በማድረግ የትራምፕ አስተዳደር ላይ ጫና መፍጠር ነው።