InternationalNews

የቀድሞው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንና ሌሎች የአውሮፓ የደህንነት ባለስልጣናት የተጓጓዙበት የባቡር መስመር ከአፍታ በኋላ በሩሲያ ጥቃት ተፈፀመበት።

የብሪታንያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአውሮፓ ህብረት የፀጥታ ባለስልጣናት በኪዬቭ አንድ ስብሰባ ላይ ሲሳተፉ ቆይተው ነው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ አደጋው የተጣለው።

ይሁንና በዲፕሎማቶች ልዑካን ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

ሩሲያ ያስወነጨፈችው ሚሳኤል ዮሆዲን ባቡር ጣቢያ በሚገኝ ሌላ የባቡር መሳቢያ ሞተር ላይ ጉዳት አድርሷል።

ሩሲያ በምዕራብ ዩክሬን የድሮን ጥቃት መፈፀሟን ገልፃ ብታልፍም የዩክሬን የባቡር ትራንስፖርት ባለስልጣናት የጥቃቱ ኢላማ ዲፕሎማቶቹ የተሳፈሩበት ባቡር ነበር ብለዋል።

የቀድሞው የሲአይኤ ኃላፊ ዴቪድ ፔትሮስ ጥቃቱ እጅግ አስደንጋጭ ነበር ብለዋል።

የዲፕሎማቶቹ ባቡር ከአደጋው ያመለጠው በሩሲያ የተሰጋ ጥቃት ቀደም ብሎ ከአካባቢው እንዲርቅ በመደረጉ ነው።