InternationalNews

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 አመት ከፍተኛ ከውጭ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) ካገኙ የአፍሪካ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ 4ኛ ደረጃ መያዟን አንድ ሪፖርት አመለከተ።

አለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ በምህፃሩ አይኤፍኤዲ ይሄን ያለው የሃገራት ከውጭ የሚላክ ገንዘብ ገቢን አስመልክቶ አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ ነው።

ድርጅቱ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 አመት 7 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ከውጭ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) ማግኘቷን እና በአፍሪካ 4ኛ ደረጃ ላይ መስፈሯን ገልጿል።

በፈረንጆቹ 2025 አመት ከፍተኛ ከውጭ የሚላክ ገንዘብ ካስገቡት የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ግብፅ በ41.5 ቢሊየን ዶላር ገቢ 1ኛ ፣ ናይጄሪያ በ22.8 ቢሊየን ዶላር ገቢ 2ኛ እና ሞሮኮ በ13.7 ቢሊየን ዶላር ገቢ 3ኛ ደረጃ መያዛቸውን ድርጅቱ ገልጿል።

አፍሪካ በፈረንጆቹ 2025 አመት ከውጭ ከተላከ ገንዘብ (ሬሚታንስ) 124 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማስገባቷ በሪፖርቱ ተገልጿል።