EthiopiaNews

ኢትዮጵያ የኮይሻ ግድብን ለማጠናቀቅ የሚያስችላትን የ400 ሚሊየን ዩሮ ብድር ለማግኘት ከ3 የጣሊያን ባንኮች እየተደራደረች መሆኑ ተነገረ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አሽብር ባልቻ የ3 ቢሊየን ዩሮ ፕሮጀክት የሆነውን የኮይሻ ግድብ ግንባታን ለመጨረስ 100 ሚሊየን ዩሮ ከሃገር ውስጥ ብድር ለማግኘት
መታቀዱን ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ከ3 የጣሊያን ባንኮች የ400 ሚሊየን ዩሮ ብድር ለማግኘት የሚያስችለው ስምምነት ጥቅምት ወር ላይ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

የኮይሻ ግድብ ሲጠናቀቅ 1ሺ 8 መቶ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው መረጃዎች ያመለክታሉ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ ትርፋማ እንዲሆን እንዳስቻለው ብሉምበርግ በዘገባው አስታውሷል።