የቴስቲ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ፈይሰል አብዶሽ (ፈይሰል አብዶሽ ሲግኔቸር ) በሚል ለአለም አቀፍ ገበያ ያቀረቡት የጉጂ ስፔሻሊቲ ቡና በአንድ ኪሎ ግራም 2,376.50 ዶላር (ከ380 ሺህ ብር በላይ) በመሸጥ ሪከርድ ማስመዝገቡ ተነገረ።
መቀመጫቸውን በእንግሊዝና በአሜሪካ ባደረጉት የኤም ካልቲቮ የኦንላይን ጨረታ መድረክ ላይ የተካሄደው ይህ ሽያጭ፣ የኢትዮጵያ ቡና ጥራትና ተሰሚነት በዓለም ገበያ ላይ እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ከዚህ ሽያጭ የሚገኘው ገቢም በቴስቲ ፋውንዴሽን አማካይነት በጉጂ ዞን ለሚገነባው የጤና ጣቢያ ግንባታ ማጠናቀቂያ እንደሚውል ተገልጿል።መረጃው ከኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የተገኘ ነው።
