EthiopiaNews

በጅዳ ተቀማጭነቱን ያደረገው ኢላፍ ራዋ ካምፓኒ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት በመመደብ በኢትዮጵያ ፔትሮሊየም በማውጣትና በማጣራት ለገበያ የማቅረብ ስራ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡

ጅዳ የሚገኘው ኢፌዲሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ይህንን ያሳወቀው የካምፓኒው የስራ ሀላፊዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ የማግባባት ስራ መስራቱን በገለጸበት መግለጫው ላይ ነው፡፡

የድርጅቱ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው በመግለጽ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል ያለው ቆንስላው ለኢንቨስትመንቱ የሚያስፈልግ ሰነዶችን ማሟላት ከተቻለ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል፡፡