EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ደንበኞች ሂሳባቸውን ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ጋር የማስተሳሰሪያ ጊዜ ገደብን እስከ ጥቅምት 30 ድረስ አራዝሟል፡፡

ባንኩ ከዚህ ቀደም በ27 የከተማ አስተዳደሮችና በሐረሪ ክልል ያሉ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6/2018 ዓ.ም፣ በቀሪው የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ደንበኞች ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ሂሳባቸውን ከፋይዳ ጋር እንዲያስተሳስሩ ሰጥቶት የነበረው ቀነ-ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ ሂሳባቸው ያላስተሳሰሩ ደንበኞች ከሂሳቡ የሚወጣ ገንዘብ እንዲታገድ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ባንኩ አሁን በሰጠው ማሳሰቢያ ደግሞ በ27ቱ ከተሞችና በሐረሪ ክልል ውጭ ላሉ ደንበኞች የነበረው የሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ቀነ-ገደብ እስከ መጪው ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን አስታውቋል።

እስካሁን ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ያላስተሳሰሩ ደንበኞች በባንክ ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ ማስተሳሰሪያ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር የተጣለውን እግድ ማስነሳት እንደሚችሉም ባንኩ ጠቅሷል፡፡