EthiopiaNews

ኩርሙክ ጎልድ ማይን የሙከራ የወርቅ ምርቱን ለማምረት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቅቆ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል።

የአላይድ ጎልድ ኮርፖሬሽን አካል የሆነው ኩርሙክ ጎልድ ማይን የመጀመሪያ የወርቅ ምርቱን ለማምረት ዝግጁ መሆኑን በይፋ ማሳወቁን የገለጸው ሚኒስቴሩ ኩባንያው ከዓመታት የፍለጋ፣ የምህንድስና እና የግንባታ ሥራዎች በኋላ የመጨረሻውን የተግባር ሙከራ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ኩርሙክ አዲስ የልማትና የምርት ምዕራፍ ውስጥ በመግባት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለዘርፉ ዕድገት አዲስ ተስፋ ይዞ እየመጣ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አክሎ ጠቅሷል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv