የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ ከኢራን ጋር በከባድ ጦርነት ውስጥ በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት፣ ለሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተመድ ስብሰባን እንዲታደሙ ቪዛ ፈቅዷል።
በዚህ ፍቃድ መሰረት የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ በሚቀጥለው ሳምንት ኒውዮርክ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው።
ሁለቱ ሀገራት በጦርነት ውስጥ በሚገኙበትና የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ባልተከፈተበት ሁኔታ ይህ ውሳኔ መተላለፉ ያልተለመደ ነው ተብሏል።
እርምጃው በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማፅያን በሳዑዲ አረቢያና በቀይ ባህር የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃታቸውን ባጠናከሩበት ወቅት የተወሰደ ነው።
አሜሪካ ምንም እንኳ የተመድ ጉባኤ አስተናጋጅ ሃገር ብትሆንም፣ የሃገራት መሪዎች ወደ ጠቅላላ ጉባኤው እንዳይመጡ የመከልከል መብቷ የተገደበ ነው የተባለ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ግን ከአሜሪካ ጋር ግጭት ውስጥ ለነበሩ መሪዎች ቪዛ የከለከለችበት ወይም ማመልከቻዎችን እንዳያስገቡ ያደረገችበት ጊዜ እንደነበር ተመልክቷል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
