ሩሲያ ቀደም ሲል ለጦር ልምምድ ይውሉ የነበሩ የመለማመጃ ሚሳኤሎችን በማሻሻል በዩክሬን ላይ የምታደርገውን የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ማጠናከሯ ተገለጸ።
አር ኤም 48 ዩ የተሰኙት እነዚህ ሚሳኤሎች በቅርብ ወራት ውስጥ ሞስኮ በዩክሬን ላይ ካስወነጨፈቻቸው የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ድርሻ ይዘዋል ነው የተባለው።
ጥቃቱ የተባባሰው ዩክሬን የሩሲያን የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ማክሸፍ የሚችለው የአሜሪካ ሰራሽ ፓትሪዮት ሚሳኤል አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ሰለተቀነሰባት መሆኑ ተገልጿል።
የመከላከያ ባለሙያዎች እንደሚሉት ሩሲያ እነዚህን አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁ ሚሳኤሎች የምትጠቀመው የዩክሬንን አየር መከላከያ ለማዳከም እና ዋና ዋና ኢስካንደር ሚሳኤሎቿን በቀጣይ ለምታደርጋቸው ዘመቻዎች ለማስቀረት ነው ተብሏል።
ይህንን አውዳሚ የአየር ጥቃት ተከትሎ በዩክሬን የንጹሃን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ፣ ኪየቭ ከምዕራባውያን አጋሮቿ አስቸኳይ የአየር መከላከያ ድጋፍ እንዲደረግላት በድጋሚ ጥሪ ማቅረቧ ነው የተሰማው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
