የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በተለይም በአረብ ሀገራት በሚኖሩና በሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች መብቶች ጥበቃ ላይ በትኩረት ለመሥራት እቅድ መያዙን አስታወቀ።
ይህ የተነገረው በህንድ ኒው ደልሂ ዓለም አቀፍ የልምምድ ልውውጥ መድረክ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው እና በምክትል ዋና ኮሚሽነር ሚዛኔ አባተ የተመራው የኢሰመኮ ልዑክ ከኦማን ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ልዑክ ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
በውይይቱ ወቅትም በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ዙሪያ በቅንጅት ለመሥራት፣ በኦማን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰብአዊ መብቶችና ደህንነት በተሻለ ሁኔታ እንዲጠበቅና ሕጋዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ እንዲሁም በሥራ ላይ የሚያጋጥሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመከላከልና የፍትሕ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ መደረሳቸው ነው የተገለጸው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
