ኢራን ሆርሙዝ ንለመክፈት ያቀረበችውን የሰላም እቅድ አሜሪካ ውድቅ ማድረጓን ተከትሎ፣ አገሪቱ ችግሩ በዲፕሎማሲያዊ ብቻ ሊፈታ እንደሚገባ አስታወቀች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ የባህር ወሽመጡን መልሶ መክፈት የሚቻለው ሀገራቸው ያቀረበችው ቅድመ ሁኔታ ሲሟላ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው ኢራን በጦርነቱ ክፉኛ እየተሸነፈች በመሆኗ ከስምምነት ለመድረስ ከፍተኛ ጉጉት እንዳላትና በቀጣይም ተጨማሪ ድርድሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
አሜሪካ የኢራንን የሰላም እቅድ ውድቅ ያደረገችው ቴህራን ማዕቀቦች አስቀድመው እንዲነሱላት በመጠየቋ እና የኒውክሌር ፕሮግራሟን በተመለከተ ለምታደርገው ድርድር እምነት ሊጣልባት ባለመቻሉ መሆኑን የተመድ የአሜሪካ ልዑክ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል፣በኢራን የሚደገፉት የሁቲ ታጣቂዎች በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረው በመቀጠላቸው፣ በሪያድ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን በበይነ መረብ ለመስጠት መገደዳቸው ተሰምቷል።
