የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ፍቃድ ያላገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስታወቂያ ከማስነገር እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል፡፡
ማንኛውም ተቋም በካምፓስ፣ በመርሀ ግብር ወይም በትምህርት መስክ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ሳያገኝ ማንኛውንም ማስታወቂያ መስራትና ማሰራጨት የተከለከለ መሆኑን ነው ባለስለጣኑ የገለጸው፡፡
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ መሠረት አሳሳች ማስታወቂያ የሚያሰራጭ ተቋምን እስከመዝጋት የሚያደርስ እርምጃ እንደሚወስድ የገለጸው ባለስልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስቧል፡፡
