የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቀደም ሲል 21 የነበሩት ዞኖች ወደ 6 ዞኖች መዋቀራቸውን አስታወቀ።
ይህ የተባለው ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው የስራ ዘመኑ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።
ጨፌው የቀረበለትን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈጻሚ አካላት የማቋቋሚያ አዋጅ አጽድቋል።
ሪፎርሙ በሕግ የተደገፈና ሥልጣንን ወደ ታች ለማውረድ ያለመ መሆኑን በመግለጽ፣ ቀደም ሲል 21 የነበሩት ዞኖች ወደ 6 ዞኖች መዋቀራቸውን ተናግረዋል።
እነዚህም ዞኖች፦የኦሮሚያ ምስራቅ ዞን ፣የኦሮሚያ ማዕከላዊ ዞን ፣ የኦሮሚያ ምዕራብ ዞን ፣የኦሮሚያ ደቡብ ዞን ፣የኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ዞን እና የኦሮሚያ ደቡብ ምስራቅ ዞን መሆናቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።
