EthiopiaNews

ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትና በባሪያ ንግድ ምክንያት ለደረሱ ጉዳቶች የካሳ ክፍያ መስጠት አስቸኳይ እና አስፈላጊ መሆኑን ገለጸች፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን የገለጸችው የፀረ ዘረኝነት፣ መድልዎ፣ መጤ ጠልነት እና ተዛማጅ አለመቻቻልን የሚያንፀባርቁ ጉዳዮችን ለመዋጋት ለፀደቀው የደርባን  ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነት በገለጸችበት ወቅት ነው፡፡

የደርባን ስምምነት እና የድርጊት መርሃ ግብር 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ለማሰብ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አዳም ተስፋዬ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትና በባሪያ ንግድ ምክንያት ለደረሱ ጉዳቶች የካሳ ክፍያ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የደርባን ስምምነት የድርጊት መርሃ ግብር በአውሮፓውያኑ በ2001 በደቡብ አፍሪካ በደርባን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የፀረ ዘረኝነት፣ መድልዎ፣ መጤ ጠልነት እና ተዛማጅ አለመቻቻልን የሚያንፀባርቁ ጉዳዮችን ለመዋጋት የፀደቀ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ስራ ላይ እንዲውል የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍም ጠቅሷል፡፡