የፋይናንስ ዘርፍ የሳይበር ደህንነት ፎረም በይፋ መመስረቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው የፋይናንስ ፎረም ላይ ይፋ የተደረገው ይህ ፎረም፤ የሀገሪቷ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እና የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ መሰረት የሆነውን የፋይናንስ ዘርፍ ከሳይበር ጥቃት የመጠበቅ እና ጠንካራ የዲጂታል ፋይናንስ ሥነ-ምህዳር የመፍጠር ዓላማ ያለው ነው ተብሏል።
ፎረሙ ባለፈው ሰኔ 2018 ዓ.ም የጸደቀውን የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅን መሠረት በማድረግ፤ በዘርፉ የሳይበር ደህንነት እርምጃዎችን በመከታተል ክፍተቶችንና የአሠራር ማነቆዎችን የሚፈታ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
