የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አድርጎ በድጋሚ ሾመ።
ምክር ቤቱ ላለፉት ስድስት ዓመታት አዲስ አበባን የመሩት አዳነች አቤቤን በድጋሜ ከንቲባ አድርጎ የሾመው ከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት በዚህ ወቅት ነው፡፡
ሹመቱን ተከትሎም ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ላለፉት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት ቡዜና አልከድር፤ እንዲሁም ምክትላቸው የነበሩት ፈይዛ መሐመድ በኃላፊነት ቦታቸው ላይ እንዲቆዩ በድጋሚ ተመርጠዋል።
