የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ ባካሄዳቸው የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎች 2.3 ቢሊየን ዶላር ለባንኮች ማቅረቡን አስታወቀ።
የባንኩ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ይሄን ያሉት በዐድዋ ድል መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ባለው ሁለተኛው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 ጉባኤ ላይ ነው፡፡
የባንኩ ገዥ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት በ20 እጥፍ ማደጉንም በመድረኩ ላይ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ቁጥጥር የሚያደርግ የተደራጀ ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ገልፀዋል።
