EthiopiaNews

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ በሚገኘው የግብፅ ኤምባሲ ውስጥ በዲፕሎማቲክ ሰራተኝነት ሲሰሩ የቆዩትን አህመድ ሞሃራም አህመድ ሶሊማንን “ተቀባይነት የሌላቸው ዲፕሎማት”በማለት ከሀገር እንዲወጡ አዟል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ውሳኔው የተላለፈውም በቪዬና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ስምምነት ድንጋጌዎች መሠረት ነው።

በዚህም ዲፕሎማቱ በ48 ሰዓታት ውስጥ ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ ተጠይቋል።