EthiopiaNews

ኢትዮጵያ በግብፅ ምክንያት የተስተጓጉሉ የውሃ ፕሮጀክቶችን ኢኮኖሚያዊ ኪሳራዎች እና ያመለጡ የልማት ዕድሎች የሚገመግም ሀገራዊ የዓባይ የካሳ ኮሚቴ ማቋቋሟን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ አስታወቁ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በግብፅ የተስተጓጎሉ ከ22 በላይ የልማት ፕሮጀክቶች በኮሚቴው ተለይተው ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

አዲስ የተቋቋመው ኮሚቴ ባለሙያዎችን፣ የቀድሞ ሚኒስትሮችን፣ አማካሪዎችን እና የህግ ባለሙያዎችን ያካተተ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ በፕሮጀክቶቹ ላይ መረጃዎችን እያጠናቀረ እና የኢትዮጵያን የካሳ ጥያቄዎች መሰረት እየመረመረ መሆኑንም ገለጸዋል፡፡