EthiopiaNews

በርዕሰ ብሔር ታዬ አጽቀሥላሴ የቀረቡ የ2019 ዓ.ም የመንግስት ዋና ዋና ትኩረቶች ፦

✅ሰላም ለኢትዮጵያ እድገት እና ብልጽግና ያለው ዋጋ ያጤነና እና ከማንኛውም ጊዜ የበለጠ ህብረትን፣ ትብብርን እና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር የሚከናወን ይሆናል።

✅ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲኖር ይደረጋል።

✅ትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከሉ ያደረገ ልማት ይፋጠናል።

✅ለእድገታችን ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪ እና የግብርና ግብአቶች እንዲሁም ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ አቅማችን ራሱን እንዲችል ይደረጋል።

✅የፕሮጀክት እና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈጻጸም ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይሰራል።

✅የታክስ መሰረትንም በማዘመን፣ ዕዳን ወግ ባለው መልኩ ማስተዳደር እንዲሁም የመንግስት ገቢ እና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም ያድጋል።

✅በፌደራል መንግስት እና በክልሎች መካከል ያለው የሰራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ኩነት የተባበረ፣ የተደጋገፈ፣ ቀልጣፋ እና እንከን አልባ እንዲሆን ይደረጋል።

✅የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ በተለይም ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የደመኝነት እይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር፣ ለቀጣናዊ ሰላም እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጥ ተነሳሽነቶች ያሉት እና አለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያሳድግ ይሆናል።