EthiopiaNews

የአለም ባንክ በፈረንጆቹ 2026 አመት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ ሃገራት አውጥቶት የነበረውን የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ከፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ባንኩ ይሄን ያለው አዲስ ባወጣው መግለጫ ነው።

ባንኩ ከ7 ወራት በፊት ለአፍሪካ ሃገራት አውጥቶት የነበረውን የ2026 አመት የ4 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገትን ወደ 4 ነጥብ 3 በመቶ ማሳደጉን ነው ያስታወቀው።

ባንኩ የአፍሪካ ሃገራት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ላይ ማሻሻያ ያደረገው የሃገራቱ የኢኮኖሚ አፈፃፀም አበረታች በመሆኑ ነው ብሏል።

የአፍሪካ ሃገራት የኢራን ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የአቅርቦት ሰንሰለት ችግሮችን መቋቋም እንደቻሉ ባንኩ ገልጿል።

ኢትዮጵያ ፣ዛምቢያ ፣ ናይጄሪያ እና አንጎላ ለአመታት እያካሄዱት ባለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሳቢያ ዘንድሮ የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘግባሉ ተብሏል።

ርዕሰ ብሔር ታዬ አፅቀ ስላሴ ዘንድሮ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ10 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ትናንት በም/ቤት ባደረጉት ንግግር መግለፃቸው ይታወሳል።

ባንኩ የአፍሪካ ሃገራት በተለይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲሰሩ አሳስቧል። መረጃው ከአለም ባንክ የተገኘ ነው።