የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው ተገልጿል።
ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የምክትል ዋና ፀሐፊዋ ጉብኝት ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እንደሆነ አምባሳደር ብርሃኑ የገለጹ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያና በተቋሙ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ተጨማሪ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት።
