ሰሞኑን ተከታታይ የሁቲዎች ጥቃት የደረሰበት የሳዑዲ አረቢያ ዋነኛ አየር ማረፊያ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግቶ ይቀመጣል ተብሏል።
የአገሪቱ የአቪየሽን ባለስልጣናት እንዳሉት ሁቲዎች የሚፈፅሙት ጥቃት በመቀጠሉ የመንገደኞችና ሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግ ሆኖ መቆየቱ አስፍፈላጊ ነው ተብሏል።
ሁቲዎች ሰሞኑን በፈፀሟቸው ጥቃቶች በትንሹ 13 ሰዎች በአየር ማረፊያው እንዳሉ ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ቆስለዋል። በርካታ አየር መንገዶችም ወደ ሪያድ መብረር ማቆማቸው ተመልክቷል።
ሁቲዎች ቀደም ብለው አየር መንገዶች የሳዑዲ አረቢያ የአየር ክልልና የአየር ማረፊያዎችን እንዳይጠቀሙ አስጠንቀቀው ነበር።
ሁቲዎች ቀደም ብለው በፈፀሙት ጥቃት ከተገደሉት 13 ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ከ300 በላይ መቁሰላቸው ይታወሳል።
